የቴክኖሎጂ ፊልዶችን ለመማር እያሰቡ ያሉ ሰዎች የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የቴክኖሎጂ ፊልዶችን ለመማር እያሰቡ ያሉ ሰዎች የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

21.090 Lượt nghe
የቴክኖሎጂ ፊልዶችን ለመማር እያሰቡ ያሉ ሰዎች የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ቴክኖሎጂ ፊልድን ለመቀላቀል እያሰቡ ያሉ ሰዎች ግልጽ ያልሆነላቸውን ጥያቄ ያቀረቡበትና በሰፊው የተወያየንበት የኦፕን ሃውስ ፕሮግራም ነበረን። ፕሮግራሙ ላይ ላልተገኛችሁና፣ ነገር ግን የቴክኖሎጂ ፊልድን ለማጥናት እያሰባችሁ ላላችሁ፣ ይህ አይነቱ ውይይት በጣም ስለሚጠቅማችሁ፣ ሙሉ ፕሮግራሙን በቪድዮ ቀርጸን አቅርበንላችሗል። በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡና መልስ ያገኙበት ሲሆን፣ ከጥያቄዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፥ 👉እኔ ምንም የኮምፒውተር ባክግራውንድ የለኝም። ሙሉ ለሙሉ ከዜሮ ነው የምጀምረው። እንደ እኔ አይነቱ ሰው የአጭር ግዜ ኮርስ ብቻ ወስዶ ወደ ቴክኖሎጂ ፊልድ መቀላቀል ይችላል? 👉የትኛውን ፊልድ ብማር የበለጠ ይመከራል? 👉የመረጥኩትን ፊልድ ኮሌጅ ገብቼ ብማር ይሻላል ወይስ አጫጭር ኮርስ ብወስድ? 👉ምን ያህል ግዜ ይወስድብኛል? 👉ስራ ስገባስ ምንድነው የሚጠበቅብኝ? 👉ሼር ፖይንትን መማር ትክክለኛ ምርጫ ነው ወይ? እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ጥያቄዎች የተመለሱበት ውይይት ስለነበር፣ እርሶም ይህንን ፕሮግራም እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል። መልካም ቆይታ